am_tn/2sa/15/32.md

2.3 KiB

እንዲህም ሆነ

ይህ ሀረግ የዋለው በታሪኩ ፍሰት ቀጣዩን ትዕይንት ለማስተዋወቅ ነው፡፡ (አዲስ ትዕይንት ማስተዋወቅ የሚለውን ይመልከቱ)

በመንገዱ ጫፍ

እዚህ ስፍራ"ጫፍ" ሚለው ቃል የዋለው ዳዊት ከታች ወደ ላይ ስለወጣ እና ወደ ኮረብታው ጫፍ ስለሄደ ነው፡፡ "ከኮረብታው ጫፍ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

እግዚአብሔር ይመለክበት በነበረበት ስፍራ

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "ሰዎች በአንድ ወቅት እግዚአብሔርን ያመልኩ በነበረበት ስፍራ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

ኩሲ

ይህ የወንድ ስም ነው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)

አርካዊ

ይህ የአንድ ወገን ህዝብ የሆኑ ስም ነው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)

ልብሱን ቀዶ እና ራሱ ላይ አፈር ነስንሶ

ይህ ሀፍረትን እና መጸጸትን የሚገልጽ ድርጊት ነው፡፡ እዚህ ስፍራ "አፈር" የሚለው "ትቢያ" ነው፡፡ "እጅግ ማዘኑን ለማሳየት ልብሱን ቀደደ፣ በራሱም ላይ ትቢያ ነሰነሰ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ትዕምርታዊ/ምልክታዊ ድርጊት እና ስኔክቲክ/ የአንድን ነገር ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ የሚሉትን ይመልከቱ)

የአኪጦፌልን ምክር ከንቱ ታደርግልኛለህ

ዳዊት ለኩሲ የአኪጦፌልን ምክር ሁሉ ከንቱ እንዲያደርግ ሀሳብ ያቀርብለታል፡፡ "የአኪጦፌልን ምክር በማፍረስ/በመቃወም ልታገለግለኝ ትችላለህ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)