am_tn/2sa/15/21.md

1.7 KiB

ህያው እግዚአብሔርን! በጌታዬ በንጉሡ ህይወት እምላለሁ

እዚህ ስፍራ ተናጋሪው ብርቱ ቃል ኪዳን ይገባል፡፡ ቃል ኪዳኑን የመጠበቁን እርግጠኝነት ከያህዌ እና ከንጉሡ ህያውነት ጋር ያነጻጽራልለ፡፡ "በያህዌ እና በንጉሡ ህይወት በጽኑ ቃል እገባለሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ተነጻጻሪ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

አገልጋይህ

እዚህ ስፍራ ኢታይ ራሱን በዚህ መንገድ የሚገልጸው ንጉሡን ለማክበር ነው፡፡

በሞትም ሆነ በህይወት

"አንተን እየደገፍኩ ብገደል እንኳን"

መላው አገር በጮኸት አለቀሰ

ብዙዎቹ የእስራኤል ሰዎች ንጉሡ ለቆ ሲወጣ በጮኸት አለቀሱ፡፡ እዚህ ይህ ማጠቃለያ የቀረበው መላው አገር አለቀሰ በሚል ነው፡፡ "በመንገድ የነበረው ህዝብ ሁሉ አለቀሰ" ወይም "ብዙ ህዝብ አለቀሰ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ኩሸት እና አጠቃላይ አስተያየት የሚሉትን ይመልከቱ)

ከፍ ባለ ድምጽ

እዚህ የሚያለቅሰው ህዝብ የተነገረው ሁሉም አንድ ከፍ ያለ ድምጽ እንደተጋሩ ተደርጎ ነው፡፡ "ጮኸው/ከፍ ባለ ድምጽ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያው አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ቄድሮን ሸለቆ

ይህ ኢየሩሳሌም አጠገብ የሚገኝ ቦታ ስም ነው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)