am_tn/2sa/15/05.md

1.4 KiB

እጁን ዘርግቶ ያቅፍና ይስም ነበር

ይህ ድርጊት የወዳጅነት ሰላምታ ነው፡፡ "በማቀፍና በመሳም እንደ ወዳጅ ሰላምታ ይሰጣል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ትዕምርታዊ/ምልክታዊ ድርጊት የሚለውን ይመልከቱ)

ፍርድ ለማግኘት

ይህ ማለት ለክርክራቸው ብይን ለማግኘት ወደ ንጉሡ ይመጣሉ፡፡ "ለክርክራቸው ብይን ለማግኘት" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

በዚህ አይነት አቤሴሎም የእስራኤልን ሰዎች ልብ ሰረቀ

የዚህ ዐረፍተ ነገር ትርጉም አቤሴሎም ሰዎች ከዳዊት ይልቅ ለእርሱ ታማኝ እንዲሆኑ ያሳምናቸው ነበር ማለት ነው፡፡ እዚህ ስፍራ ጸሐፊው እርሱ ልባቸውን ሰረቀ በማለት ሰዎች እንዴት ለአቤሴሎም ታማኝ እንደሆኑ ይናገራል፡፡ "አቤሴሎም በዚህ መንገድ የእስረኤል ሰዎች ለእርሱ ታማኝ እንዲሆኑ አሳመናቸው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)