am_tn/2sa/15/03.md

1.5 KiB

አቤሴሎምም ያንን ሰው እንዲህ ይለው ነበር

ሰውየው ለአቤሴሎም ጉዳዩን እንደሚናገር በውስጠ ታዋቂነት ተጠቅሷል፡፡ ይህ ግልጽ ተደርጎ ሊጻፍ ይችላል፡፡ "አቤሴሎም ሰውየውን ችግሩ ምን እንደሆነ ይጠይቀዋል፣ ከዚያም ሰውየው ፍትህ እንደሚፈልግ ለአቤሴሎም አብራርቶ ይናገራል፡፡ ከዚያም አቤሴለም ለሰውየው እንዲህ ይላል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

መልካም እና ትክክል

እነዚህ ቃላት በመሰረቱ ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው በአንድነት የዋሉት የእርሱ ጉዳይ መልካም እንደሆነ ትኩረት ሰጥቶ ለመግለጽ ነው፡፡ (ጥንድ ትርጉም የሚለውን ይመልከቱ)

ጉዳይህን ለመስማት

ጉዳይን "መስማት" ማለት ነገሩን መስማት እና በዚያ ላይ የውሳኔ ፍርድ መስጠት ማለት ነው፡፡ "ጉዳይህን ለመበየን/በጉዳይህ ላይ ፍርድ ለመስጠት" ወይም "የአንተን ጉዳይ ከላይ ሆኖ ለማየት" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)