am_tn/2sa/13/30.md

1.5 KiB

ስለዚህም እንዲህ ሆነ

"እንዲህም ሆነ፡፡" እዚህ ስፍራ ይህ ሀረግ የዋለው በታሪኩ ፍሰት ቀጣዩን ትዕይንት ለማስተዋወቅ ነው፡፡ (አዲስ ትዕይንትን ማስተዋወቅ የሚለውን ይመልከቱ)

በመንገድ ላይ

"በመንገድ በመጓዝ ላይ"

እንዲህ የሚል ወሬ ወደ ዳዊት ደረሰ

እዚህ ላይ አንድ ሰው በእርግጥ ደርሷ ለዳዊት ወሬውን ሲነግረው ወሬው ደረሰ ይላል፡፡ "አንድ ሰው መጥቶ ወሬውን ለዳዊት እንዲህ ሲል ነገረው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

ከዚያም ንጉሡ ተነሳ

"ከዚያ ንጉሡ ተነስቶ ቆመ"

ልብሱን ቀደደ፣ በምድርም ላይ ወደቀ

እነዚህን ነገሮች ያደረገው እጅግ ማዘኑን ለመግለጽ ነው፡፡ "ልብሱን ቀደደ፣ አምርሮ በማዘን ምድር ላይ ወደቀ" (ትዕምርታዊ/ምልክታዊ ድርጊት የሚለውን ይመልከቱ)

ልብሶቻቸውን ቀደዱ

እነርሱ ይህንን ያደረጉት ሀዘናቸውን ለመግለጽ እና ከንጉሱ ጋር ለማዘን ነው፡፡ "ልብሶቻቸውንም ቀደዱ፣ ከንጉሱ ጋር አዘኑ" (ትዕምርታዊ/ምልክታዊ ድርጊት የሚለውን ይመልከቱ)