am_tn/2sa/13/27.md

2.8 KiB

አቤሴሎም ዳዊትን ተጫነው/አጥብቆ ጠየቀው

እዚህ ስፍራ ጸሐፊው አቤሴሎም አብሯቸው እንዲሄድ ዳዊት ይፈቅድ ዘንድ አምኖን የጠየቀበትን ሁኔታ በእርሱ ላይ አካላዊ ጫና እንዳሳረፈ አድርጎ ያቀርበዋል፡፡ "አቤሴሎም አምኖን ይመጣ ዘንድ ዳዊትን ለመነው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

አትፍሩ

ይህ የሚያመለክተው አምኖንን በመግዳላቸው ሊከተል የሚችለው ውጤት ሊያስፈራቸው እንደማይገባ ነው፡፡ ይህ በግልጽ ሊጻፍ ይችላል፡፡ "የንጉሱን ልጅ በመግደላችሁ እንወነጀላለን ብላችሁ አትፍሩ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

ያዘዝኳችሁ እኔ አይደለሁምን?

አቤሴሎም ይህንን ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚጠይቀው ለአምኖን መገደል እርሱ ተጠያቂ እንደሚሆን ትኩረት ሰጥቶ ለመግለጽ ነው፤ ምክንያቱም ያዘዛቸው እርሱ ነው፡፡ ይህ በዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "ይህን አንድታደርጉ ያዘዝኳችሁ እኔ ነኝ" ወይም "ለእርሱ መግደል ተጠያቂ የምሆነው እኔ ነኝ ምክንያቱም ይህን እንድታደርጉ እኔ አዝዣችኋለሁ፡፡" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ እና ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚሉትን ይመልከቱ)

እናንተን አላዘዝኳችሁም

አቤሴሎም ያደርጉት ዘንድ እነርሱን ያዘዘው ነገር በጥያቄው ውስጥ ሊገለጽ ይችላል፡፡ "እርሱን እንድትገድሉት አላዘዝኳችሁም" (የተዘለለ/የተተወ የሚለውን ይመልከቱ)

የንጉሱ ወንዶች ልጆች ሁሉ

ይህ የሞቱትን አቤሴሎምን እና አምኖንን አይጨምርም፡፡ ይህ የሚያካትተው ወደ ድግሱ እንዲሄዱ ንጉሱ የፈቀደላቸውን የተቀሩትን ወንድ ልጆች ነው፡፡ "የተቀሩት የንጉሱ ወንድ ልጆች" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ስኔክቲክ/ የአንድን ነገር ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ የሚለውን ይመልከቱ)

እያንዳንዱ ሰው

ይህ የሚያመለክተው ድግሱን ትተው የወጡትን የንጉሱን ወንዶች ልጆች ነው፡፡