am_tn/2sa/13/01.md

1.2 KiB

ከዚህም በኋላ እንዲህ ሆነ

"ከዚህ በኋላ እንዲህ ሆነ፡፡" ይህ ሀረግ የዋለው በታሪኩ ፍሰት አዲስ ትዕይንትን ለማስተዋወቅ ነው፡፡ (አዲስ ትዕይንትን ማስተዋወቅ የሚለውን ይመልከቱ)

ግማሽ እህት/በአባት ወይም በእናት ብቻ የሚገኛኙ

አምኖን እና ትዕማር አባታቸው አንድ ሲሆን በእናት ይለያያሉ

ሙሉ እህት/በአባትና በእናት የሚገናኙ

አቤሴሎም እና ትዕማር በአባትም በእናትም ይገናኛሉ

አምኖን በእህቱ በትዕማር ምክንያት እስኪታመም ድረስ እጅግ ተረብሾ ነበር

አምኖን የተረበሸው ከእህቱ ከትዕማር ጋር ለመተኛት ፍላጎት ስለነበረው ነው፡፡ "አምኖን ለእህቱ ትዕማር በነበረው ፍላጎት ህመም እስኪሰማው ድረስ እጅግ ተረብሾ ነበር" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)