am_tn/2sa/11/24.md

1.8 KiB

አጭሩ ውርወራቸው

"አጭር የሚባለው የቀስት ውርወራቸው"

ጥቂት የንጉሱ ወታደሮች ተገደሉ

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "ጥቂቶቹን የንጉሱን አገልጋዮች ገደሉ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

የንጉሱ አገልጋዮች

እዚህ ስፍራ "አገልጋዮች" የሚለው የሚያመለክተው ወታደሮችን አንጂ ባሮችን አይደለም፣ ምክንያቱም ወታደሮች የንጉሱ አገልጋዮች ነበሩ፡፡

አገልጋይህ ኬጢያዊው ኦርዮን ተገድሏል

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "አገልጋይህን ኬጢያዊውን ኦርዮንን ገድለውታል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

ሰይፍ ይህንን ያንንም ይበላል

እዚህ ስፍራ "ሰይፍ" የሚለው የሚያመለክተው በሰይፍ አንድን ሰው የሚገድልን ሰው ነው፡፡ እንደዚሁም ደግሞ፣ አንድን ሰው በሰይፍ መግደል የተገለጸው ሰይፍ ሰዎችን "እንደሚበላ" ተደርጎ ነው፡፡ "አንደኛው ሰው በሰይፍ እንደሚገደል ሌላኛውም ሊገደል ይችላል" ወይም "በጦርነት ውስጥ ማንኛውም ሰው ሊሞት ይችላል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት እና ዘይቤያዊ አነጋገር የሚሉትን ይመልከቱ)

ውጊያህን ይበልጥ አጠንክረው

"ይበልጥ ጠንክረህ ተዋጋ"