am_tn/2sa/11/21.md

2.0 KiB

የሩቤ-ሼትን ልጅ አቤሜሌክን የገደለው ማን ነው?

ኢዮአብ ዳዊት እነዚህን ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄዎች በመጠየቅ ይገስጸኛል ብሎ ነበር፡፡ ይህ በዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ " የሩቤ-ሼት ልጅ አቤሜሌክ እንዴት እንደተገደለ አስታውስ!" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

የሩቤ-ሼት ልጅ አቤሜሌክ

ይህ የወንድ ስም ነው፡፡ አባቱ ጌድዮን በሚባልም ስም ይታወቅ ነበር፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)

አንዲት ሴት በቴቤስ ከግንቡ የወፍጮ መጅ በጣለችበት ወቅት ሰውየው አልሞተምን?

ኢዮአብ ዳዊት እነዚህን ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄዎች በመጠየቅ ይገስጸኛል ብሎ ነበር፡፡ ይህ በዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "በቴቤስ ከግንቡ አናት ላይ ሆና የወፍጮ መጅ ስትጥልበት ሰውየው እንደሞተ አስታውሱ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

የወፍጮ መጅ

ከባድ ድንጋይ፣ እህል ለመፍጨት የሚያገለግል

ከግንቡ

"ከከተማዋ ግንብ አናት"

ቴቤስ

ይህ የአንዲት ከተማ ስም ነው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)

ለምን ወደ ግንቡ ይህን ያህል እጅግ ተጠጋችሁ?

ኢዮአብ ዳዊት እነዚህን ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄዎች በመጠየቅ ይገስጸኛል ብሎ ነበር፡፡ ይህ በዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "ወደ ግንቡ ይህን ያህል እጅግ መጠጋት አልነበረባችሁም!" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)