am_tn/2sa/11/18.md

1.6 KiB

ኢዮአብ ለዳዊት ቃል/ መልዕክት ላከ

"ቃል ላከ" የሚለው ሀረግ የሆነውን ለማድረስ መልዕክት ላከ ማለት ነው፡፡ "ኢዮአብ የሆነውን ለዳዊት ለማድረስ መልዕክት ላከ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

ለምን ወደ ግንቡ … ይህን ያህል ተጠጋችሁ?

ኢዮአብ ዳዊት እነዚህን ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄዎች በመጠየቅ ይገስጸኛል ብሎ ነበር፡፡ እነዚህ ጥያቄዎች በዐረፍተ ነገር ሊጻፉ ይችላሉ፡፡ "ለመዋጋት ይህንን ያህል ወደ ከተማይቱ መቅረብ አልነበረባችሁም፡፡ በግንቡ ላይ ሆነው እንደሚመቷችሁ ማወቅ ነበረባችሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

ከግንቡ ሆነው እንደሚወረውሩ

ይህ የሚያመለክተው የከተማዋ ሰዎች በከተማዋ ግንብ አናት ላይ ሆነው ወደ ጠላቶቻቸው ቁልቁል ቀስታቸውን እንደሚወረውሩ ነው፡፡ "ከከተማዋ ግንብ አናት ላይ ሆነው ቀስቶቻቸውን በእናንተ ላይ እንደሚወረውሩ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)