am_tn/2sa/11/09.md

2.4 KiB

የእርሱ ጌታ

"የእርሱ" የሚለው ቃል ኦርዮን ያመለክታል፤ "ጌታ" የሚለው ደግሞ ዳዊትን ያመለክታል፡፡

የመጣኸው ከመንገድ አይደለምን? ስለምን ወደ ቤትህ አትወርድም/አትሄድም?

ይህ ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የዋለው ኦርዮን ሚስቱ ለማየት መሄድን መቃወሙን ለማጉላት ነው፤ ሃሳቡ በዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "ከእንዲህ አይነት ረጅም መንገድ ከመጣህ በኋላ፣ አሁን ወደ ቤትህ መውረድ አለብህ " በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

እስራል እና ይሁዳ

ይህ ሰራዊታቸውን ያመለክታል፡፡ "የእስራኤል እና የይሁዳ ሰራዊቶች" (ስኔክቲክ/ የአንድን ነገር ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ የሚለውን ይመልከቱ)

ከሚስቴ ጋር …. እንዴት ወደ ቤቴ መሄድ ይሆንልኛል?

ይህ ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የዋለው ኦርዮ ሚስቱን ለማየት መሄዱን መቃወሙን ለማጉላት ነው፤ ይህ በዐረፍተ ነገር ሊተረጎም ይችላል፡፡ "በሰራዊቴ ውስጥ የሚገኙት ሌሎች ወታደሮች በአደጋ ላይ ሆነው ከሚስቴ ጋር ለመሆን…ወደ ቤቴ መሄድ በደል መፈጸም ይሆንብኛል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ እና ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚሉትን ይመልከቱ)

በህያው ነፍስህ እምላለሁ፣ ይህንን በፍጹም አላደርገውም

ኦርዮ ሌሎች ወታደሮች በጦርነት ላይ እያሉ ወደ ቤቱ ሚስቱ ዘንድ እንደማይሄድ ጠንካራ የቃል ኪዳን መሃላ ያደርጋል፡፡ ይህን ቃል ኪዳን የሚያደርገው የቃል ኪዳኑን እውነተኛነት ከንጉሱ ህያውነት እርግጠኝነት ጋር በማነጻጸር ነው፡፡ " ይህንን እንደማላደርገው በጽኑ ቃል እገባለሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ተነጻጻሪ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)