am_tn/2sa/11/06.md

2.2 KiB

ከዚያም ዳዊት ላከ

እዚህ ስፍራ "ላከ" የሚለው ዳዊት መልዕክተኛ ላከ ማለት ነው፡፡ "ከዚየም ዳዊት መልዕክተኛ ላከ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ኢዮአብ እንዴት እንደሆነ፣ ሰራዊቱ ምን እያደረገ እንደሆነ፣ እና ጦርነቱ እንዴት እየተካሄደ እንደ ነበር

ዳዊት ኢዮአብ እና ሰራዊቱ ደህና ስለ መሆናቸው እና ስለ ጦርነቱ አካሄድ ይጠይቅ ነበር፡፡ "ኢዮአብ ደህና ከሆነ፣ ሌሎች ወታደሮችም ደህና ከሆኑ፣ ደግሞም ጦርነቱ እንዴት እየተካሄደ እንደሆነ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ወደ ቤትህ ውረድ

"ወደ ታች ውረድ" ለሚለው ሀረግ ሊሰጡ የሚችሉ ትርጉሞች 1) የኦርዮ ቤት ከንጉሱ ቤተ መንግስት ዝቅ ባለ ስፍራ ላይ ይገኝ ነበር ወይም 2) የኦርዮ ቤት ከንጉሱ ቤተ መንግስት ይልቅ ያነሰ ጠቃሚነት ነበረው፡፡ "ወደ ቤትህ ሂድ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

እግርህን ታጠብ

ይህ ሀረግ ከእለት ስራ በኋላ ምሽቱን ለማረፍ ወደ ቤት መመለስ ለሚለው ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት/ ነው፡፡ "ምሽቱን እረፍ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

ንጉሱ ለኦርዮ ስጦታ ላከለት

ዳዊት ለኦርዮ ስጦታውን እንዲያመጣለት አንድ ሰው ላከ፡፡ ይህ በግልጽ ሊጻፍ ይችላል፡፡ "ንጉሱ ለኦርዮ ስጦታ እንዲወሰድለት አንድ ሰው ላከ" (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)