am_tn/2sa/11/01.md

1.1 KiB

በፀደይ ወቅት እንዲህ አጋጠመ

"በፀደይ ወቅት ይህ ሆነ፡፡" ይህ በታሪኩ ፍሰት አዲስ ትዕይንትን ያስተዋውቃል፡፡ (አዲስ ትዕይንትን ማስተዋወቅ የሚለውን ይመልከቱ)

በጊዜው

"በአመቱ ወቅት"

ዳዊት ኢዮአብን፣ አገልጋዮቹን እና መላውን የእስራኤል ሰራዊት ላከ

ዳዊት እነርሱን ወደ ጦርነት ላከ፡፡ ይህ ግልጽ ተደርጎ ሊጻፍ ይችላል፡፡ እንደዚሁም "የእርሱ" የሚለው ቃል ዳዊትን ያመለክታል፡፡ "ዳዊት ኢዮአብን፣ አገልጋዮቹን፣ እና መላውን የእስራኤል ሰራዊት ወደ ጦርነት ላከ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡(ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

የአሞን ሰራዊት

"የአሞናውያን ሰራዊት"

ረባት

ይህ የከተማ ስም ነው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)