am_tn/2sa/09/11.md

2.0 KiB

የአንተ ባሮች ጌታዬ ንጉሡ ባሮቹን ያዘዘውን ሁሉ ያደርጋሉ

ሲባ ራሱን "የአንተ ባሪያ" በማለት ሲገልጽ ዳዊትን ደግሞ " የእኔ ጌታ" በማለት ይናገራል፡፡ "እኔ፣ የአንተ ባሪያ አንተ ንጉሴ አደርገው ዘንድ ያዘዝከኝን ሁሉ አደርጋለሁ" (አንደኛ፣ ሁለተኛ ወይም ሶስተኛ መደብ የሚለውን ይመልከቱ)

ሚካ

ይህ የሜምፊቦስቴ ልጅ ስም ነወ፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)

በሲባ ቤት የሚኖሩ ሁሉ

እዚህ ስፍራ "ቤት" የሚለው የሚወክለው የሲባን ቤተሰብ ነው፡፡ "መላው የሲባ ቤተሰብ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

እርሱ ሁሌም ከንጉሱ ገበታ ይበላ ነበር

እዚህ ስፍራ "ገበታ" የሚለው የሚወክለው ሁሌም ከዳዊት ጋር አብሮ መሆንን ወይም ከእርሱ ጋር መገኘትን ነው፡፡ ከንጉሱ ጋር ሆኖ ከገባታው መብላት ታላቅ ክብር ነበር፡፡ "ሁሌም ከንጉሱ ጋር ሆኖ ከገበታው ይበላ ነበር" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

ምንም እንኳን ሁለቱም እግሮቹ ሽባ ቢሆኑም

"ምንም እንኳን ሁለቱም እግሮቹ የተጎዱ ቢሆኑም፡፡" እዚህ ስፍራ "እግር" የሚለው የሚወክለው መራመድ መቻልን ነው፡፡ "መራመድ የማይችል ቢሆንም" በሚለው ውስጥ አንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)