am_tn/2sa/09/07.md

1.8 KiB

ዮናታን፣ ለአባትህ ስል

"ዮናታን፣ አባትህን ስለምወደው"

ሁልጊዜም ከገበታዬ ትበላለህ

እዚህ ስፍራ "ገበታዬ" የሚለው የሚወክለው ከዳዊት ጋር አብሮ መሆንን ወይም የእርሱን መገኘት/አብሮነት ነው፡፡ ከንጉሱ ጋር በገበታው ቀርቦ መብላት ታላቅ ክብር ነበር፡፡ "ሁሌም ከእኔ ጋር አብረህ ትቀርባለህ/ትበላለህ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

እንደ ሞተ ውሻ የሆንኩትን ባሪያህን በሞገስ ትመለከተኝ ዘንድ ባሪያህ ምንድን ነው?

ይህ ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ ሜምፊቦስቴ ንጉሱ እርሱን ይንከባከበው ዘንድ የሚያበቃው ነገር እንደሌለው መረዳቱን ያሳያል፡፡ ይህ በዐረፍተ ነገር ሊተረጎም ይችላል፡፡ "እኔ እንደ ሞተ ውሻ ነኝ፡፡ ደግነትን ልታሳየኝ የተገባሁ አይደለሁም፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

የሞተ ውሻ የምመስል

እዚህ ስፍራ ሜምፊቦስቴ የሳኦልን ትውልድ ይወክላል፣ ደግሞም ራሱን "ከሞተ ውሻ" ጋር ያነጻጽራል፡፡ ውሾች እንደ ቤት እንስሳ የማይቆጠሩ፣ እንክብካቤ የማይደረግላቸው እና ጥቅማቸው ይህ ነው የማይባሉ እንስሳት ነበሩ፡፡ የሞተ ውሻ ከዚህ ይልቅ የማይረባ ተደርጎ ይወሰዳል፡፡ "እንደ እኔ ያለው እንደ ሞተ ውሻ እርባና የሌለው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)