am_tn/2sa/07/27.md

2.3 KiB

ለባሪያህ ቤት ትሰራለታለህ

ዳዊት ራሱን "የአንተ ባሪያ" እያለ ይጠቅሳል/ያመለክታል፡፡ "ለእኔ ቤት ትሰራልኛለህ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አንደኛ፣ ሁለተኛ፣ ወይም ሶስተኛ መደብ የሚለውን ይመልከቱ)

ለእርሱ ቤት ትሰራለታለህ

እዚህ ስፍራ "ቤት" የሚለው ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት/ የሚያመለክተው የዳዊት ትውልድ የእስራኤል መሪ ሆኖ እንደሚቀጥል ነው፡፡ በ 2ሳሙኤል 7፡4 ያህዌ ዳዊትን እርሱ የያህዌን ቤት የሚሰራ መሆኑን ይጠይቀዋል፡፡ በዚያ ስፍራ "ቤት" የሚለው ቃል የሚወክለው ቤተመቅደስን ነው፡፡ በቋንቋችሁ ሁለቱንም ሃሳቦች የሚገልጽ ቃል ካለ በዚህ ስፍራ እና በ 2ሳሙኤል 7፡4 ላይ ያንን ቃል ተጠቀሙ፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

አሁን

ይህ "በዚህን ጊዜ" ማለት አይደለም፣ ነገር ግን ለቀጣዩ ጠቃሚ ነጥብ ትኩረት ለመስጠት ውሏል፡፡

ቃሎችህ የታመኑ ናቸው

"እኔ አንተ የምትናገረውን አምናለሁ"

በአንተ በረከት የባሪያህ ቤት ለዘለዓለም የተባረከ ይሆናል

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "አንተ ቤቴን ለዘለዓለም መባረክህን ትቀጥላለህ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

የባሪያህ ቤት

እዚህ ስፍራ ዳዊት ራሱን "የአንተ ባሪያ" በማለት ይገልጻል፡፡" "የእኔ ቤት" ወይም "የእኔ ቤተሰብ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አንደኛ፣ ሁለተኛ፣ ወይም ሶስተኛ መደብ የሚለውን ይመልከቱ)

ቤት

እዚህ ስፍራ "ቤት" የሚለው ቃል የሚወክለው የዳዊትን ቤተሰብ ነው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)