am_tn/2sa/07/24.md

2.0 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ዳዊት ከያህዌ ጋር መነጋገሩን ቀጠለ፡፡

ስለዚህ አሁን

እዚህ ስፍራ "አሁን" የሚለው "በዚህን ጊዜ" ማለት አይደለም፡፡ ነገር ግን ወደ ተከታዩ ጠቃሚ ነጥብ ትኩረትን ለመሳብ ውሏል፡፡

ለባሪያህ እና ለቤቱ የገባኸው ቃል ኪዳን ለዘለዓለም የጸና ይሁን

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "ለእኔ እና ለቤቴ የገባኸውን ቃል ኪዳን ፈጽመው፣ ቃል ኪዳንህም ለዘላለም የጸና ይሁን" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

ባሪያህ እና ቤተሰቡ/ቤቱ

ዳዊት ስለ ራሱ በሶስተኛ መደብ እየተናገረ ነው፡፡ ይህ በአንደኛ መደብ ሊጻፍ ይችላል፡፡ "እኔ እና የእኔ ቤት" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አንደኛ፣ ሁለተኛ፣ ወይም ሶስተኛ መደብ የሚለውን ይመልከቱ)

ስምህ ለዘለዓለም ታላቅ ይሁን

እዚህ ስፍራ "ስም" የሚወክለው የያህዌን ክብር ነው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

የእኔ የባሪያህ፣ የዳዊት ቤት

እዚህ ስፍራ "ቤት" የሚለው የሚወክለው ቤተሰብን ነው፡፡ "የእኔ ቤተሰብ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

በፊትህ የጸና ነው

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "ከአንተ የተነሳ የተጠበቀ ነው" ወይም "ከአንተ የተነሳ ይቀጥላል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)