am_tn/2sa/07/21.md

2.7 KiB

ስለ ቃልህ ስትል

"ልታደርግ ቃል በገባኸው ምክንያት"

የራስህን አላማ ልትፈጽም

"ልታደርግ ያቀድከውን ለመፈጸም"

ለባሪያህ

ዳዊት ራሱን "የአንተ ባሪያ፡፡" በማለት ይገልጻል፡፡ ይህ በመጀመሪያ መደብ ሊጻፍ ይችላል፡፡ "ለ እኔ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አንደኛ፣ ሁለተኛ፣ ወይም ሶስተኛ መደብ የሚለውን ይመልከቱ)

እኛ በገዛ ጆሮቻችን እንደ ሰማነው

"በገዛ ጆሮቻችን" የሚለው ሀረግ የዋለው ትኩረት ለመስጠት ነው፡፡ "እኛ ራሳችን እንደ ሰማነው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

እኛ እንደ ሰማነው

እዚህ ስፍራ "እኛ" የሚለው የሚያመለክተው ዳዊትን እና የእስራኤልን ህዝብ ነው፡፡ (የሚያካትት እና የማያካትት "እኛ" የሚለውን ይመልከቱ)

እስራኤል እንዳንተ ያለ ህዝብ ማን ነው፣ አምላኩ እግዚአብሔር ሄዶ ያዳነው በምድር ላይ ብቸኛ ህዝብ እንዳንተ ማን ነው?

ዳዊት ይህንን ጥያቄ የተጠቀመው፣ እንደ እስራል ያለ ሌላ ህዝብ እንደሌለ ትኩረት ለመስጠት ነው፡፡ "እስራኤል እንዳንተ ያለ ሌላ ህዝብ የለም፣ እግዚአብሔር ለራሱ ሄዶ በምድር ላይ ያዳነው አንድ ህዝብ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

ለራስህ ስም የለየኸው

እዚህ ስፍራ "ስም" የሚወክለው የያህዌን ክብር ነው፡፡ "ሁሉም ህዝብ አንተ ማን እንደሆንክ እንዲያውቅ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

ለምድርህ

እዚህ ስፍራ "ምድር" የሚወክለው ህዝብን ነው፡፡ "ለአንተ ህዝብ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

አንድ ወገን ህዝብ አባረርህ

እዚህ ስፍራ "ህዝብ" የሚለው የሚወክለው በከነዓን ይኖሩ የነበሩ ሰዎችን ወገን ነው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)