am_tn/2sa/07/18.md

2.0 KiB

ያህዌ አምላክ፤ እስከዚህ ደረጃ ያደረስከኝ፣ እኔ ማን ነኝ፣ ቤቴስ ምንድን ነው?

ዳዊት ይህንን ጥያቄ የሚጠይቀው የያህዌን አዋጅ ሲሰማ የተሰማውን ጥልቅ ስሜት ለመግለጽ ነው፡፡ ይህ ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ በዐረፍተ ነገር መልክ ሊተረጎም ይችላል፡፡ " ያህዌ አምላክ ሆይ፣ እኔ እና ቤተሰቤ ለዚህ ክብር የተገባን አይደለንም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

በአንተ ዐይኖች ፊት/በፊትህ

እዚህ ስፍራ እይታ የሚወክለው ፍርድን ወይም ሚዛንን ነው፡፡ "በአንተ ፍርድ/ሚዛን" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

የአንተ ባሮች ቤተሰብ

እዚህ ስፍራ ዳዊት ራሱን "የአንተ ባሪያ" በማለት ይገልጻል፡፡ ይህ በመጀመሪያ መደብ ሊገለጽ ይችላል፡፡ "የእኔ ቤተሰብ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አንደኛ፣ ሁለተኛ፣ ወይም ሶስተኛ መደብ የሚለውን ይመልከቱ)

በሚመጣው ታላቅ ጊዜ

ይህ የሚናገረው ስለ ጊዜ ነው፤ ጊዜ እየተጓዘ እንደሚመጣ እና አንድ ስፍራ እንደሚደርስ ነገር ተደርጎ ተገልጽዋል፡፡ "እና ወደፊት በእነርሱ ላይ ምን ይሆናል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

የአንተ ባርያ

እዚህ ስፍራ ዳዊት ራሱን "የአንተ ባሪያ" በማለት ይገልጻል፡፡ ይህ በመጀመሪያ መደብ ሊገለጽ ይችላል፡፡ "የእኔ ቤተሰብ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አንደኛ፣ ሁለተኛ፣ ወይም ሶስተኛ መደብ የሚለውን ይመልከቱ)