am_tn/2sa/07/15.md

3.0 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

ያህዌ በነቢዩ ናታን በኩል ለንጉሥ ዳዊት ቃል ኪዳኑን መግለጹን አጠናቀቀ

የቃል ኪዳኔ ታማኝነት ከሳኦል እንደራቀ፣ ከእርሱ ግን አልወስድበትም

"ታማኝነት" የሚለው ቃል "በታማኝነት ወዳጅ" እንደሚለው ረቂቅ ስም ነው፡፡ "ሳኦልን መውደዴን እንዳቋረጥኩት፣ እርሱን በታማኝነት መውደዴን በፍጹም አላቋርጥም"በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)

ከአንተ በፊት፡፡ የአንተ ቤት… ከአንተ በፊት ፡፡ የአንተ ዙፋን

በ 2ሳሙኤል7፡8-9 ቀጥተኛ ጥቅስን ቀጥተኛ ባልሆነ ጥቅስ ተርጉማችሁ ከሆነ፣ አሁን እዚህ ላይ "አንተ" የሚለውን "ዳዊት" ወይም "እርሱ" ወይም "የእርሱ" ብላችሁ በዩዲቢ እንደሚገኘው መተረጎም ሊያስፈልጋችሁ ይችላል፡፡ "ከዳዊት በፊት፡፡ የዳዊት ቤት… ከእርሱ በፊት፡፡ የእርሱ ዙፋን" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቀጥተኛ እና ቀጥተኛ ያልሆነ ጥቅሶች የሚለውን ይመልከቱ)

ቤትህ እና መንግስትህ በፊትህ ለዘለዓለም የጸና ይሆናል፡፡ ዙፋንህ ለዘለዓለም ይመሰረታል፡፡

እነዚህ ሁለት ዐረፍተ ነገሮች ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው፤ ደግሞም የዳዊት ስርወ መንግስት ለዘለዓለም እንደሚጸና ያጎላሉ፡፡(ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ቤትህ እና መንግስትህ በፊትህ ለዘለዓለም የጸና ይሆናል፡፡

እዚህ ስፍራ "ቤት" የሚለው ቃል፣ ንጉስ ሆኖ የሚገዛውን የዳዊትን ትውልድ ይወክላል፡፡ እዚህ "መንግስት" ማለት "ቤት" የማለት ያህል ተመሳሳይ ነገር ነው፡፡ ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ጭምር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "ቤተሰብህን ሳጸና እና እነርሱ በእስራኤል ላይ ለዘለዓለም ሲገዙ ትመለከታለህ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ጥንድ ትርጉም እና አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚሉትን ይመልከቱ)

ዙፋንህ ለዘለዓለም ይመሰረታል፡፡

እዚህ "ዙፋን" የሚወክለው ንጉስ ሆኖ የመግዛት ሃይልን ነው፡፡ "ትውልድህ በእስራኤል ላይ ለዘለዓለም እንዲገዛ አደርጋለሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

እነዚህ ቃላት ሁሉ

"እነዚህ ነገሮች ሁሉ፡፡" ይህ ያህዌ የተናገረውን ያመለክታል፡፡

ስለ ጠቅላላው ራዕይ ነገረው

"ያህዌ ለእርሱ ስለ ገለጠለት ነገር ሁሉ ነገረው