am_tn/2sa/07/12.md

2.7 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

ያህዌ በነቢዩ ናታን በኩል ለንጉሥ ዳዊት ቃል ኪዳኑን መግለጹን ቀጠለ

ቀናቶቻችሁ ሲያበቁ እና ከአባቶቻችሁ ጋር ስታሸልቡ

እነዚህ ሁለት ሀረጋት ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው የተጣመሩት ትኩረት ለመስጠት ነው፡፡ ሁለቱም አገላለጾች ሞትን በተሻሉ ቃላት የሚገልጹ ናቸው፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ እና ዩፊሚዝም/ የማያስደስትን ቃል ሻል ባለ ቃል መተካት የሚለውን ይመልከቱ)

ከአንተ በኋላ ትውልድ አስነሳለሁ

ያህዌ የዳዊትን ትውልድ መሾሙ የተገለጸው ያህዌ እርሱን እንደሚያነሳቀው ወይም ከፍ እንደሚያደርገው ተደርጎ ነው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ከአብራክህ የሚወጣው

ይፍ ፈሊጣዊ አነጋገር ሲሆን ሰውየው የዳዊት ትውልድ ነው ማለት ነው፡፡ (ፈሊጣው አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

መንግስቱን አጸናለሁ

እዚህ ስፍራ "መንግስቱ" የሚለው የሚወክለው የመግዛት ሀይሉን ነው፡፡ "በጣም ሃያል ንጉሥ እንዲሆን አደርገዋለሁ" (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

ለእኔ ስም ቤት

እዚህ ስፍራ "ስም" የሚያመለክተው ያህዌን ነው፡፡ "ለእኔ የዘለዓለም/ቋሚ መኖሪያ" (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

የመንግሥቱን ዙፋን ለዘለዓለም እገነባለሁ

እዚህ ስፍራ "ዙፋን" የሚወክለው የሰውየውን እንደ ንጉሥ የመግዛት ሃይል ነው፡፡ "ግዛቱ በእስራኤል ለዘለዓለም እንዲጸና አደርጋለሁ" (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

እኔ ለእርሱ አባት እሆናለሁ፣ እርሱም ልጄ ይሆናል

በ 2ሳሙኤል7፡12-14 የቀረበው ትንቢት የዳዊትን ልጅ ሰለሞንን ይመለከታል፡፡ ነገር ግን የትንቢቱ ገጽታዎች የሚሟሉት በኢየሱስ ነው፡፡ ስለዚህ፣ እዚህ ስፍራ "አባት" እና "ልጅ" የሚሉትን ቃላት በቋንቋችሁ በሚገኘው የስጋ አባትእና ልጅ የተለመደው ቃል መተረጎሙ ይመረጣል፡፡