am_tn/2sa/07/10.md

3.3 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

ያህዌ በነቢዩ ናታን በኩል ለንጉሥ ዳዊት ቃል ኪዳኑን መግለጹን ቀጠለ

እኔ ቦታ እሰጣለሁ

"እኔ ቦታ እመርጣለሁ"

በዚያ እተክላቸዋለሁ

ያህዌ ህዝቡን በምድሪቱ በቋሚነት ማኖሩ እና ጥበቃው የተገለጸው በምድሪቱ እንደሚተክላቸው ተደርጎ ነው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ከእንግዲህ አትጨነቁም/አትቸገሩም

ይህ በአድርጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "ማንም ከእንግዲህ አያስጨንቃቸውም" (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

ከቀናቱ አንስቶ

"ከጊዜው አንስቶ"

ዳኞችን አዛለሁ

የእስራኤል ህዝብ ወደ ከነዓን ምድር ከገባ በኋላ እና የሚገዛቸው ንጉሥ ከማግኘታቸው በፊት፣ እግዚአብሔር "ዳኞች/ፈራጆች" ተብለው የሚጠሩ መሪዎችን በችግራቸው ጊዜ እንዲመሯቸው ይሾምላቸው ነበር፡፡

በህዝቤ በእስራኤል ላይ እንዲሆኑ

በስልጣን መሆን የተገለጸው በአንድ ሰው ላይ የበላይ መሆን ተብሎ ነው፡፡ "ህዝቤን እስራኤልን እንዲመሩ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

አሁን ከጠላቶቻችሁ ሁሉ አሳርፋችኋለሁ… ቤት እንደምሰራላችሁ በእርግጥ እነግራችኋለሁ፡፡

በ 2ሳሙኤል 7፡8-9 ቀጥተኛውን ጥቅስ፣ ቀጥተኛ ባልሆነ ጥቅስ ተርጉማችሁ ከሆነ፤ እዚህ ስፍራ "አንተ" የሚለውን "እርሱ" ወይም "የእርሱ" ብላችሁ መተርጎም ሊያስፈልግ ይችላል፡፡ "አሁን ከጠላቶቹ ሁሉ አሳርፈዋለሁ… ቤት እንደምሰራለት በእርግጥ እነግረዋለሁ" (በጥቅስ ውስጥ የሚገኝ ጥቅስ እና ቀጥተኛ እና ቀጥተኛ ያልሆኑ ጥቅሶች)

ከጠላቶቻችሁ ሁሉ አሳርፋችኋለሁ

"ከጠላቶቻችሁ ሁሉ እጠብቃችኋለሁ" እዚህ ስፍራ "እረፍት" የሚለው ረቂቅ ስም ነው፡፡ "ጠላቶቻችሁ ሁሉ እንንተን ማጥቃት እንዲያቆሙ አደርጋለሁ" (ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)

ቤት እሰራልሃለሁ

እዚህ ስፍራ "ቤት" የሚለው ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት/ የሚያመለክተው የዳዊት ትውልዶች የእስራኤል መሪ ሆነው እንደሚቀጥሉ ነው፡፡ በ 2ሳሙኤል 7፡4 ያህዌ ዳዊትን እርሱ የያህዌ ቤትን የሚሰራ መሆኑን ይጠይቀዋል፡፡ በዚያ ስፍራ "ቤት" የሚለው ቃል የሚወከወለው ቤተመቅደስን ነው፡፡ ቋንቋችሁ ሁለቱንም ሃሳቦች የሚገለጽ ቃል ካለው በዚህ ስፍራ እና በ 2ሳሙኤል 7፡4 ላይ ተጠቀሙበት፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)