am_tn/2sa/07/08.md

2.8 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

ያህዌ ቃል ኪዳኑን ለንጉሥ ዳዊት በነብዩ ናታን በኩል ይገልጥለታል፡፡

አሁን

ይህ "በዚህን ጊዜ" ማለት አይደለም፣ ነገር ግን ለቀጣዩ ጠቃሚ ነጥብ ትኩረት ለመስጠት ውሏል፡፡

ለባሪያዬ ለዳዊት፣ "የሰራዊት ጌታ ያህዌ የሚለው ይህንን ነው፡ ‘እኔ አነሳሁህ… ስምህን ከፍ አደርገዋለሁ፣ በምድር ላይ ስማቸው ታላቅ እንደሆኑት ታላቅ አደርግሃለሁ' በለው፡፡

ይህ በጥቅስ ውስጥ ጥቅስ ይዟል፡፡ ቀጥተኛ የሆነውን ጥቅስ በዩዲቢ ውስጥ እንደሚገኘው ቀጥተኛ ባልሆነ ጥቅስ መተገረጎሙ አስፈላጊ ሊሆን ይችላል፡፡ "ለባሪያዩ ለዳዊት እኔ እንዳነሳሁት… ስሙን ከፍ ታላቅ እንዳደረግኩት፣ በምድር ላይ ስማቸው ታላቅ እንደሆኑት ታላላቆች እንዳደረኩት ንገረው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (በጥቅስ ውስጥ ጥቅስ እና ቀጥተኛ እና ቀጥተኛ ያልሆነ ጥቅሶች የሚሉትን ይመልከቱ)

ለባሪያዬ ለዳዊት እንዲህ በለው

ያህዌ ለነብዩ ናታን አሁንም ለዳዊት መናገር ያለበትን እየነገረው ነው

ለግጦሽ ከምታሰማራበት ስፍራ አነሳሁህ

የዳዊት የእረኝነት ስራ የተገለጸው በጎቹን በሚጠብቅበት ስፍራ ነው፡፡ "እረኛ ከነበርክበት ስፍራ አነሳሁህ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

እኔ ከአንተ ጋር ነበርኩ

እዚህ ስፍራ "ከአንተ ጋር" የሚለው ያህዌ ዳዊትን ረድቶታል ደግሞም ባርኮታል ማለት ነው፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ጠላቶችህን ሁሉ እቆርጣለሁ

የያህዌ የዳዊትን ጠላቶች መደምሰስ የተገለጸው፣ አንድ ሰው የልብስ ቁራጭን እንደሚቆርጥ ወይም ከዛፍ ላይ ቅርንጫፉን እንደሚቆርጥ ያህዌ የዳዊትን ጠላቶች እንደቆረጣቸው ተደርጎ ነው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ስምህን ታላቅ አደርገዋለሁ

እዚህ ስፍራ "ስም" የሚለው የሚወክለው ክብርን ነው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

ታላላቆች

"ታላላቆች" የሚለው ሀረግ ዝነኛ ሰዎች ማለት ነው፡፡