am_tn/2sa/07/06.md

1.9 KiB

ለየትኛው ህዝቤን እንዲመራልኝ ለቀባሁት የእስራኤል መሪ ‘ለምን ቤት አልሰራችሁልኝም?' በማለት ተናግሬያለሁን?"

ይህ በጥያቄ ውስጥ ጥያቄ ይዟል፡፡ ቀጥተኛው ጥቅስ ቀጥተኛ ያልሆነ ጥቅስ ተደርጎ መጻፍ ይችላል፡፡ "እስራኤልን እንዲመራ ከቀባሁት መሪ ውስጥ የትኛውን መሪ ለምን የዝግባ ቤት አልሰራህልኝም ስል የጠየቅኩት አለን?" (በጥቅስ ውስጥ ጥቅስ እና ቀጥተኛ እና ቀጥተኛ ያልሆነ ጥቅሶች የሚሉትን ይመልከቱ)

ለየትኛው የእስራኤል መሪ ምን ነገር ተናግሬ አውቃለሁ

ያህዌ በፍጹም የትኛውንም የእስራኤል መሪ ቤት እንዲሰራለት እንዳልጠየቀ ትኩረት ለመስጠት ይህንን ጥያቄ ተጠቅሟል፡፡ "ለየትኛውም የእስራኤል መሪ በፍጹም ምንም ነገር አላልኩም" (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

ህዝቤን እስራኤልን እንዲጠብቅ ለቀባሁት

የእስራኤል ህዝብ መሪዎች የተገለጹት እረኞች እንደሆኑ እና ህዝቡ ደግሞ የተገለጸው በግ ተደርጎ ነው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ለምን የጥድ ቤት አልሰራችሁልኝም?

ያህዌ መሪዎቹን ይህንን ጥያቄ ጠይቋቸው ቢሆን ኖሮ፣ የጥድ ቤት ስላልሰሩለት የሚገስጽ ጥያቄ ይጠቀም ነበር፡፡ ነገር ግን፣ ያህዌ አስቀድሞ ይህንን ጥያቄ እንዳልጠየቃቸው ተናግሯል፡፡ "የጥድ ቤት ልትሰሩልኝ ይገባል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)