am_tn/2sa/06/21.md

1.9 KiB

ከአንቺ አባት በላይ እንድሆን የመረጠኝ ማን ነው

እዚህ ስፍራ "የአንቺ" የሚለው የሚያመለክተው ሜልኮልን ነው፡፡ (አንተ የሚለውን ቃል መልኮች ይመልከቱ)

በያህዌ ህዝብ ላይ፣ በእስራኤል ላይ

እዚህ ስፍራ "የያህዌ ህዝብ" እና "እስራኤል" የሚሉት ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው፡፡ (ጥንድ ትርጉም የሚለውን ይመልከቱ)

ከዚህም ይልቅ ክብሬን እጥላለሁ

ዳዊት ምጸታዊ እየሆነ ነው፤ በቃላት ከተናገረው ተቃራኒውን እየገለጸ ነው፡፡ በእርግጥ ያደረገው ነገር የሚያወርድ ነገር ነው ብሎ አይምንም ወይም ወደፊትም ወራዳ ተግባር አደርጋለሁ እያለ አይደለም፡፡ (ምፀት ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

በራሴ ዐይኖች ፊት ራሴን አዋርዳለሁ

እዚህ ስፍራ "በራሴ ዐይኖች ፊት" የሚለው የሚወክለው አንድ ሰው ስለ አንድ ነገር ስፍራ የሚሰጠውን ወይም የሚያስበውን ነው፡፡ "ራሴን ዝቅ አደርጋለሁ" ወይም "ራሴን ሞኝ እንደሆነ ሰው እቆጥራለሁ" (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

ነገር ግን አንቺ ባልሻቸው በእነዚህ ባሪያ ልጃገረዶች ዘንድ እከበራለሁ

ይህ አድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "አንቺ ያልሻቸው ባሪያ ልጃገረዶች ያከብሩኛል" (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

እሰከ ዕለተ ሞቷ ድረስ ልጅ አልነበራትም

"አንድም ልጅ ለመውለድ አልቻለችም ነበር"