am_tn/2sa/06/20.md

1.2 KiB

ወደ ውጭ መውጣት

እዚህ ስፍራ "መምጣት" የሚለው "መሄድ" ተብሎ ሊተረጎም ይችላል፡፡ (መሄድ እና መምጣት የሚሉትን ይመልከቱ)

ዛሬ የእስራኤል ነጉሥ እንዴት ከበረ

ይህ ምፀታዊ አነጋገር ነው፡፡ ሚልኮል ተቃራኒውን ማለቷ ነበር፣ ዳዊት ያደረገው የሚያስከብረውን ነገር ነው ብላ አላመነችም፡፡ ሜልኮል ንጉሥ ዳዊት ሲጨፍር የታየበትን አለባበስ እና ባህሪይ የተናገረችው በማቃለል ነበር፡፡ (ምፀት ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

በባሪያ ልጃገረዶች ዐይኖች ፊት

እዚህ ስፍራ "የባሪያ ልጃገረዶች ዐይኖች" የሚወክለው ባሪያ ልጃገረዶችን ነው፡፡ "በባሪያ ልጃገረዶች ፊት" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ስኔክቲክ/ የአንድን ነገር ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ የሚለውን ይመልከቱ)

ባለጌ ተራሰው

ሜልኮል ዳዊትን ያነጻጸረችው ከባለጌ እና ሞኝ ሰዎች ጋር ነው