am_tn/2sa/06/03.md

1.7 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

ዳዊት እና የእስራኤል ህዝብ ሰራዊት የቃል ኪዳኑን ታቦት አመጡ/አንቀሳቀሱ

አሚናዳብ…ዖዛ…አሒዮ

እነዚህ የወንድ ስሞች ናቸው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)

መላው የእስራኤል ቤት

ይህ ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት/ የሚወክለው የእስራኤልን ህዝብ ነው፡፡ "ከእርሱ ጋር የነበሩ ሌሎች እስራኤላውያን ሁሉ" (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

ታምቡሪኒ/ከበሮ መሰል የሙዚቃ መሳሪያ

ታምቡሪኒ ከአናቱ ከበሮ የሚመስል በዙሪያው ቁርጥራጭ ብረታ ብረት ያሉት ሲመታ ወይም ሲያርገፈግፉት ሙዚቃዊ ድምጽ የሚሰጥ መሳሪያ ነው፡፡ (ያልታወቁትን መተርጎም የሚለውን ይመልከቱ)

ራትል/ የቅል ቅርጽ ያለው የሚንሽዋሽዋ /ጽናጽል መሰል የሙዚቃ መሳሪያ

በሽፋን ውስጥ የሚገኝና ጠጣር የሆኑ ነገሮች በውስጡ የያዘ ሲርገፈገፍ ዜማዊ ድምጽ የሚሰጥ የሙዚቃ መሳሪያ፡፡ (ያልታወቁትን መተርጎም የሚለውን ይመልከቱ)

ሲምባል/ ሙዚቃ ማጀቢያ ሳህን መሰል የሙዚቃ መሳሪያ

ሁለት ስስ፣ ክብ የብረት ሳህን መሰል የሙዚቃ መሳሪያ ሲሆን ሲጋጭ ከፍ ያለ ሙዚቃዊ ድምጽ ይሰጣል