am_tn/2sa/06/01.md

2.6 KiB

አሁን

ይህ ቃል የታሪኩን አዲስ ክፍል ያመለክታል

የተመረጡ የእስራኤል ወንዶች በሙሉ

ይህ ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት/የእስራኤልን ሰራዊት ይወክላል፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

ሰላሳ ሺህ

"30,000" (ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)

ከይሁዳ በአል የእግዚአብሔርን ታቦት ለማምጣት

ታቦቱን ወደ ኢየሩሳሌም እንደሚወስዱ ተጠቁሟል፡፡ "ይሁዳ ውስጥ ከምትገኘው በኣላ የእግዚአብሔርን ታቦት ወደ ኢየሩሳሌም ለመውሰድ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

ከዚያ የእግዚአብሔርን ታቦት ለማምጣት

ኢየሩሳሌም ከሞላ ጎደል ከሁሉም ሌሎች የእስራኤል ስፍራዎች ከፍ ያለች ናት፣ ስለዚህ ለእስራኤላውያን ወደ ኢየሩሳሌም እንውጣ ወይም ከእርሷ እንውረድ ማለት የተለመደ ነበር፡፡

ወደ ላይ ማምጣት

"ማምጣት" የሚለው ቃል "መውሰድ" ተብሎ ሊተረጎም ይችላል፡፡ (መሄድ እና መምጣት የሚሉትን ይመልከቱ)

በአል

ይህ የቦታ ስም ነው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)

በሰራዊት ጌታ በያህዌ ስም የተጠራ

የያህዌ ስም በታቦቱ ላይ ተጽፎ ነበር

ከኪሩቤል በላይ በዙፋኑ የተቀመጠው

ኪሩብ በቃል ኪዳኑ ታቦት መክደኛ ላይ የሚገኙ መሆናቸውን ግልጽ ማድረግ ሊያስፈልግ ይችላል፡፡ የመጸሐፍ ቅዱስ ጸሐፍት ብዙውን ጊዜ የቃል ኪዳኑ ታቦት፣ በላይ በሰማይ በዙፋኑ የተቀመጠው የያህዌ እግሮች ማረፊያ እንደሆነ አድርገው ይናገራሉ፡፡ "በቃል ኪዳኑ ታቦት ከኪሩብ በላይ በዙፋኑ የተቀመጠው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

በዙፋኑ ላይ የተቀመጠው/የነገሰው

በዙፋን ላይ መቀመጥ