am_tn/2sa/05/24.md

1.0 KiB

ስትሰሙ… የፍልስጥኤም ሰራዊትን ለመጥቃት ያህዌ በፊታችሁ ይሄዳል

ይህ በ 2ሳሙኤል 5፡23 ላይ ያህዌ ለዳዊት መስጠት የጀመረው ትዕዛዝ ቀጣይ ክፈል ነው፡፡ በዚህ ስፍራ ያህዌ ስለ ራሱ በሶስተኛ መደብ ይናገራል፡፡ (አንደኛ፣ ሁለተኛ፣ ወይም ሶስተኛ መደብ የሚሉትን ይመልከቱ)

በበለሳም እንጨቶች አናት ላይ በሚነፍሰው ንፋስ የሰልፍ ድምጽ ስትሰሙ

ይህ የሚናገረው ነፋስ በቅጠሎች መሃል ሲያልፍ እንደሚያሰማው አይነት የሰልፈኛ ድምጽ ስለ መስማት ነው፡፡ "ነፋስ በበለሳም ዛፎች አናት ላይ ሰልፈኞች እንደሚያሰሙት ድምጽ ሲነፍስ" (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይምልከቱ)

ገባዖን… ጌዝር

እነዚህ የቦታ ስሞች ናቸው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)