am_tn/2sa/04/04.md

1.4 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

ይህ ሀረግ ዋናውን ታሪክ ቆም አድርጎ በኢያቡስቴ በኩል ሳይሆን በዮናታን በኩል የሳኦል ትውልድ ስለሆነው ስለ ሜምፊቦስቴ የመረጃ ዳራ ይሰጣል፡፡ ሜምፊቦስቴ ቆየት ብሎ በመጽሐፉ ውስጥ ትልቅ ገጸ ባህሪ ይሆናል፡፡ (የመረጃ ዳራ እና አዲስ እና ነባር ተሳታፊዎችን ማስተዋወቅ የሚሉትን ይመልከቱ)

እግሩ ሽባ የሆነ

ይህ ሀረግ "መራመድ የማይችል" ማለት ነው፡፡

ዕድሜው አምስት አመት

ይህ አባቱ በሞተ ጊዜ የዮናታን ልጅ ዕድሜ ነበር፡፡ (ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)

ስለ ሳኦል እና ዮናታን የተነገሩ ወሬዎች

ይህ የሚያመለክተው ስለ ሞታቸው የተነገረውን ወሬ ነው

ሞግዚት/ነርስ

ትንሽ ልጅን ለመንከባከብ የምትቀጠር ሴት ወይም ልጃገረድ

ሽባ ሆነ

ይህ ሜምፊቦስቴ እንዴት እንደተጎዳ እና መራመድ የማይችል እንደሆነ ይገልጻል፡፡

ሜምፊቦስቴ

ይህ የሳኦል የልጅ ልጅ፣ የዮናታን ወጣት ወንድ ልጅ ስም ነው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)