am_tn/2sa/04/01.md

1.5 KiB

ኢያቡስቴ… በዓና…ሬካብ…ሬሞን

እነዚህ የወንድ ስሞች ናቸው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)

እጆቹ ደከሙ

በዚህ ሀረግ "እጆቹ" የሚለው የሚወከወለው ኢያቡሰቴን ነው፡፡ "ኢያቡስቴ ደካማ ሆነ" ወይም "ኢያቡስቴ አቅሙን በሙሉ አጣ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ስኔክቲክ/ የአንድን ነገር ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ የሚለውን ይመልከቱ)

በዚህን ጊዜ…የሳኦል ልጅ ሁለት ሰዎች ነበሩት

ይህ በዓና እና ሬካብ የተባሉ ሰዎችን ወደ ታሪኩ ያስተዋውቃል፡፡ (አዲስ እና ነባር ተሳታፊዎችን ማስተዋወቅ የሚለውን ይመልከቱ)

ብኤሮት ጭምር የብንያም ክፍል ተደርጎ ስለተወሰደ፣ እና ብኤሮታውያን ወደ ጌቴም ስለሸሹ እስከ ዛሬ ድረስ በዚያ ይኖራሉ

እዚህ ስፍራ ላይ ጸሐፊው ስለ ብኤሮት ለአንባቢ የመረጃ ዳራ ይሰጣል፡፡ የብኤሮት ግዛት የብንያም ነገድ ምድር ክፍል ነበር፡፡ (የመረጃ ዳራ የሚለውን ይመልከቱ)

ብኤሮት ጌቴም

እነዚህ የቦታ ስሞች ናቸው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)