am_tn/2sa/03/33.md

1.9 KiB

አበኔር ሰነፍ እንደሚሞት መሞት አለበትን

ይህ ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የዋለው ሞቱ አግባብ የሌለው መሆኑን ትኩረት ለመስጠት ነው፡፡ "አበኔር በውርደት መሞት አልነበረበትም!" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

እጆችህ አልታሰሩም፡፡ እግሮችህም በሰንሰለት አልተያዙም

እነዚህ ሁለት ዐረፍተ ነገሮች ተመሳሳይ ሃሳብን ይገልጻሉ፡፡ በአንድ ዐረፍተ ነገር ውስጥ ሊቀርቡ ይችላሉ፡፡ "በማናቸውም መንገድ በእስርቤት ያለህ ወንጀለኛ አልነበርክም" ወይም "ሙሉ ለሙሉ ከስህተት ንጹህ ነበርክ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

እጆችህ አልታሰሩም ነበር

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "ማንም እጆችህን አላሰረም ነበር" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

እግሮችህ አልታሰሩም ነበር

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "ማንም እግሮችህን በሰንሰለት አላሰረም ነበር" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

የፍትህ አልባነት ልጆች

ይህ የሚያመለክተው ፍትህ አልባ የሆኑ ሰዎችን ወይም ክፉዎችን ነው፡፡ "ክፉ ሰዎች"በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)