am_tn/2sa/03/27.md

1.2 KiB

የበሩ መግቢያ መሃል

ይህ የሚያመለክተው በኬብሮን በከተማይቱ ቅጥር ካሉት በሮች አንዱን ነው፡፡በዩዲቢ ትርጉም ውስጥ እንደተመለከተው የከተማ በሮች የተገነቡት በከተማይቱ ቅጥር እንደሚገኙ ግንቦች ክፍል ሆነው ነው፡፡ በመተላለፊያ መንገዶቹ አጠገብ ወደ እንግዶች መቀበያ እና ንግድ እንዲሁም የፍትህ ስርአቶች ወደ ሚካሄዱባቸው ክፍሎች የሚወስዱ በሮች ይገኛሉ፡፡ ኢዮአብ አበኔርን የገደለው ምናልባት ከእነዚህ ክፍሎች በአንደኛው ነው፡፡

የአሣኤል ደም

እዚህ ስፍራ "ደም" የሚለው ቃል የተያያዘው ከአሣኤል ሞት ጋር ነው፡፡ "የአሣኤል ሞት" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

አሣኤል

ይህ ወንድ የሆነ ሰው ስም ነው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)