am_tn/2sa/03/08.md

2.0 KiB

እኔ ለይሁዳ የምወግን፣ የውሻ ራስ ነኝን?

አበኔር ስለ ራሱ፣ እስራኤላውያን ለመገበው ታማኝ ነው ብለው እንደሚቆጥሩት ውሻ ሁሉ እርሱ የውሻ ራስ ተደርጎ እንደተቆጠረ ይናገራል፡፡ እዚህ ስፍራ "ለይሁዳ መሆን" የሚለው የሚያመለክተው አቤኔር ዳዊት ለሚገኝበት ለይሁዳ እንጂ ለሳኦል ቤት አለመቆጠሩን ነው፡፡ "እኔ ክጄ ለይሁዳ ሆንኩን?" ወይም "እኔ ለዳዊት የምሰራ ከሃዲ አይደለሁም!" (ዘይቤያዊ አነጋገር እና ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚሉትን ይመልከቱ)

በዳዊት እጅ ላይ

እዚህ ስፍራ "እጅ" የሚለው የሚወክለው ለማሸነፍ ያለን አቅም ነው፡፡ "በዳዊት መሸነፍ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

ነገር ግን አንተ አሁን ይህችን ሴት በሚመለከት ጥፋተኛ አድርገህ ትከሰኛለህ?

አበኔር ይህንን ጥያቄ የሚያነሳው ኢያቡስቴን ለመገሰጽ ነው፡፡ አቤኔር በእርግጥ ከሪጽፋ ጋር ስለ መተኛቱ ወይም በሃሰት ስለመወንጀሉ ግልጽ የሆነ ነገር የለም፡፡ ሊሰጡ የሚችሉ ትርጔሜዎች እነዚህ ናቸው፡ 1) አበኔር ጥፋተኛ የሚሆነው፡ "ከዚህች ሴት ጋር በመተኛቴ ልትበሳጭ አይገባህም!" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው ወይም 2) አበኔር ጥፋተኛ የማይሆነው፡ "ከዚህች ሴት ጋር ተኝተሃል ብለህ ልታስብ አይገባህም!" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)