am_tn/2sa/03/06.md

1.9 KiB

እንዲህም ሆነ

ይህ በዳዊት ደጋፊዎች እና በሳኦል ቤት ትግል ታሪክ አካሄድ አዲስ ትዕይንትን ያስተዋውቃል፡፡ (አዲስ ትዕይንትን ማስተዋወቅ የሚለውን ይመልከቱ)

የሳኦል ቤት

ይህ ከሳኦል ቤት እና ደጋፊዎች መሃል ከሳኦል ሞት በኋላ ማን ርስቱን መቆጣጠር ይገባኛል እንደሚል የሚያመለክት ነው

የዳዊት ቤት

ይህ የዳዊትን ደጋፊዎች የሚያመለክት ነው፡፡

ከሳኦል ቤት አቤኔር ራሱን አበረታ

የአቤኔር በሳኦል ቤት ላይ ሃይሉን እየጨመረ መሄድ የተገለጸው፣ ልክ በአካል ጠንካራ እየሆነ እንደመጣ ተደርጎ ነው፡፡ "አቤኔር በሳኦል ቤት እና ደጋፊዎች ላይ የበለጠ ሃይል አገኘ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ሪጽፋ…አኪ

እነዚህ የሴቶች ስሞች ናቸው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)

ኢያቡስቴ

ይህ የወንድ ስም ነው፤ የሳኦል ልጅ ነው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)

ከአባቴ ቁባት ጋር ለምን ተኛህ?

ኢያቡስቴ ይህንን ጥያቄ የጠየቀው እንደ ንጉሥ ራሱን የቆጠረውን አቤኔርን ለመገሰጽ ነበር፡፡ "ከአባቴ ቁባት ጋር ለመተኛት መብት የለህም!" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

አብረህ ተኛህ

ይህ ለወሲባዊ ግንኙነት ዩፊሚዝም/ የማያስደስትን ቃል ሻል ባለ ቃል መተካት/ ነው፡፡