am_tn/2sa/02/26.md

2.9 KiB

አቤኔር ተጣራ

"አቤኔር ጮኸ"

ሰይፍ ለዘለዓለም ያጠፋልን?

ይህ ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ አጉልቶ የሚያሳየው ጦርነቱ እጅግ ለረጅም ጊዜ መቆየቱን ነው፡፡ እዚህ ስፍራ "ሰይፍ" የሚያመለክተው ጦርነቱን ነው፡፡ በጦርነቱ ውስጥ የተካሄደው ግድያ የተገለጸው ወታደሮቹን የዱር አውሬ እንደበላቸው ተደርጎ ነው፡፡ "ሰይፎቻችንን እርስ በእርስ ለመዋጋት እና ለመገዳደል መጠቀማችንን መቀጠል የለብንም" (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ እና ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪ በመነሳት ለአንድ ነገር ስያሜ መስጠት እንዲሁም ዘይቤያዊ አነጋገር የሚሉትን ይመልከቱ)

በመጨረሻ ይህ መራራ እንደሚሆን አታውቅምን?

ይህ ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የተራዘመ ጦርነት ለበለጠ መከራ እንደሚዳርግ ኢዮአብ እውቅና እንዲሰጥ ለማስገደድ ውሏል፡፡ እዚህ ስፍራ "መራራ" የሚለው ቃል እጅግ አሰቃቂ የሆነን መከራ ለመግለጽ የዋለዩፊሚዝም/ የማያስደስትን ቃል ሻል ባለ ቃል መተካት/ ነው፡፡ " ይህ ከቀጠለ እጅግ የከፋ ችግር እንደመሆን በሚገባ ታውቃለህ!" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ እና ዩፊሚዝም/ የማያስደስትን ቃል ሻል ባለ ቃል መተካት የሚሉትን ይመልከቱ)

የአንተ ሰዎች ወንድሞቻቸውን ከማሳደድ ይመለሱ ዘንድ የማትናገረው እስከ መቼ ድረስ ነው?

ይህ ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ ኢዮአብ እስራኤላውያን ወገኖቻቸውን መውጋት እንዲያቆም ለማሳመን የታቀደ ነው፡፡ እዚህ ስፍራ "ወንድም" የሚለው ቃል የዋለው የእስራኤል አገር ሰዎችን ለመወከል ነው፡፡ "እስራኤላውያን እርስ በእርሳቸው እንዳይገዳደሉ አሁን ይህንን አቁም!" (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ እና ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚሉትን ይመልከቱ)

ሕያው እግዚአብሔርን!

ይህ በጣም ጠንካራ መሃላ ነው፡፡ "እግዚአብሔር ምስክሬ ነው" ወይም "እግዚአብሔር ያልኩት እውነት መሆኑን ያጸናል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡

ያንን ካልተናገርክ … እስከ ማለዳ ወንድሞቻቸውን ያሳዱ

አቤኔር ለኢዮአብ በጥበብ ካልመለሰለት፣ ይህ መላምታዊ ሃሳብ ሊሆን የሚችለውን ነገር ያስረዳል፡፡ (መላምታዊ ሁኔታዎች የሚለውን ይመልከቱ)