am_tn/2sa/01/21.md

2.0 KiB

የጊልቦዓ ተራሮች

ዳዊት የእርሱን እንጉርጉሮ እንደሚሰሙት አድርጎ በቀጥታ ለ"ጊልቦዓ ተራሮች" ይናገራል፡፡ (አፖስተሮፊ የሚለውን ይመልከቱ)

ጠልም ሆነ ዝናብ አይገኝባችሁ

ዳዊት ንጉሥ ሳኦል በጦርነት የሞተበትን ምድር ይረግማል፣ ይህ የሚያደርገው እግዚአብሔር ለቀባው ነጉሥ ካለው ታላቅ አክብሮት/ውዳሴ የተነሳ ነው

የሃያላኑ ጋሻ ረከሰ

እዚህ ስፍራ "ሃያል" የሚለው የሚያመለክተው ሳኦልን ነው፡፡ ጋሻው የረከሰበት ምክንያት ምድር ላይ በመውደቁ እና የንጉሡ ደም በላዩ ስለፈሰሰበት ነበር፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

የሳኦል ጋሻ ከእንግዲህ በዘይት አይቀባም

የሳኦል ጋሻ ከቆዳ የተሰራ ነበር፡፡ ጋሻውን ለመንከባከብ በዘይት ይወለወል ነበር፡፡ "ከእንግዲህ ለሳኦል ጋሻ ማንም ግድ አይለውም"

ከተገደሉት የፈሰሰው ደምና ከታላላቆቹ አካል የዮናታን ቀስት ወደ ኋላ አላለም፣ ደግሞም የሳኦል ሰይፍ ባዶውን አይመለሰም

ሳኦል እና ዮናታን እዚህ ስፍራ ላይ የቀረቡት ብርቱ እና እጅግ ጀግና ተዋጊዎች ሆነው ነው፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

የሳኦል ሰይፍ ባዶውን አይመለሰም

የሳኦል ሰይፍ የተገለጸው በገዛ ራሱ መመለስ እንደሚችል ህይወት እንዳለው ነገር ሆኖ ነው፡፡ ባዶውን ከመመለስ ይልቅ፣ የገደላቸውን የሳኦልን ጠላቶች ደም ይዞ ይመጣ ነበር፡፡ (ሰውኛ ዘይቤ እና ምፀት የሚሉትን ይመልከቱ)