am_tn/2sa/01/17.md

2.9 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

ዳዊት ለሳኦልና ለዮናታን የሀዘን እንጉርጉሮ ተቀኘ

የቀስት እንጉርጉሮ

ይህ የእንጉርጉሮው ርእስ ነበር

በያሻር መጽሐፍ የተጻፈ ነበር

ይህ ለአንባቢው ወደፊት ምን ተደርጎ እንደነበር እንዲያውቅ በዝማሬው ላይ ተጨማሪ የመረጃ ዳራ ሆኖ የተጻፈ ነው፡፡ (የመረጃ ዳራ የሚለውን ይመልከቱ) የያሻር መጽሐፍ "ያሻር" የሚለው ቃል ትርጉሙ "ቀጥተኛ/በተጠንቀቅ" ማለት ነው፡፡ "የውጊያ ውሎ" መጽሐፍ በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)

የአንተ ክብር፣እስራኤል፣ ሞቷል

"የአንተ ክብር" የሚለው ሳኦልን ያመለክታል፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

ሃያሉ

"ሃያል" የሚለው ሀረግ ሳኦልን እና ዮናታንን ሁለቱንም ያመለክታል፡፡ ይህ ስማዊ ቅጽል የብዙ ቁጥር ነው፤ "ሃያላኑ" ተብሎ ሊገለጽም ይችላል፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት እና ስማዊ ቅጽል የሚሉትን ይመልከቱ)

ወደቀ

"ወደቀ" የሚለው ቃል በዚህ ስፍራ "ሞተ" ማለት ነው፡፡ (ዩፊሚዝም/ የማያስደስትን ቃል ሻል ባለ ቃል መተካት የሚለውን ይመልከቱ)

ይህንን በጌት አትናገሩ… በአስቀሎና መንገዶችም አታውጁ

እነዚህ ሁለት ሀረጋት ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው፤ የተደገሙትም የግጥሙ እንጉርጉሮ ክፍል ሆነው ነው፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ጌት…አስቀሎና

ጌት እና አስቀሎና ከፍልስጥኤማውያን ታላላቅ ከተሞች ሁለቱ ናቸው፡፡ ሳኦልን እና ዮናታንን የገደሉት ፍልስጥኤማውያን ናቸው፡፡

የፍልስጥኤም ሴት ልጆች ሃሴት እንዳያደርጉ… ያልተገረዙት ሴት ልጆች ክብረ በዓል እንዳያደርጉ

እነዚህ ሁለት ሀረጋት ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው፤የተደገሙትም የግጥሙ ክፍል ሆነው ነው፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ያልተገረዙት ሴት ልጆች

ይህ ሀረግ የሚያመለክተው እንደ ፍልስጥኤማውያን ያሉትን ያህዌን የማይከተሉ ህዝቦችን ነው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)