am_tn/2sa/01/08.md

1.3 KiB

‘ማን ነህ?' አለኝ፡፡ እኔም እንዲህ ብዬ መለስኩለት፣ ‘እኔ አማሌቃዊ ነኝ፡፡'

ይህ ቀጥተኛ ጥቅስ በርቱዕ/ቀጥተኛ ንግግር ሊገለጽ ይችላል፡፡ "ማን እንደሆንኩ ጠየቀኝ፣ እኔም አማሌቃዊ እንደሆንኩ ነገርኩት" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቀጥተኛ እና ቀጥተኛ ያልሆነ ጥቅሶች የሚለውን ይመልከቱ)

እኔ አማሌቃዊ ነኝ

እነዚህ ህዝቦች ዳዊት በ2 ሳሙኤል 1፡1 ላይ ድል ያደረጋቸው እነዚያው ሰዎች ናቸው፡፡

ታላቅ መከራ አገኘኝ

የሳኦል መከራ የተገለጸው አንዳች አስጨናቂ ነገር አንቆ እንደያዘው ተደርጎ ነው፡፡ "እጅግ ተጨነቅኩ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሰውኛ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ህይወቴ ገና አላለፈችም/ነፍሴ አልወጣችም

ይህ ፈሊጥ ትረጉሙ እርሱ ገና በህይወት አለ ማለት ነው፡፡ "እስከ አሁን በህይወት አለሁ" (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ከወደቀ በኋላ በህይወት አይቀጥልም

"መሞቱ አይቀርም"