am_tn/2ki/25/01.md

1.3 KiB

በዘጠነኛው ዓመት

(የቁጥር አጻጻፍ ይመልከቱ)

በዐሥረኛው ወር፣ ከወሩም በዐሥረኛው ቀን

ይህ ዐሥረኛ ወር በዕብራውያን ቀን አቆጣጠር ነው፡፡ በምዕራባውያን ቀን መቁጠሪያ ዐሥረኛው ቀን ታህሣሥ መጨረሻ ላይ ነው፡፡ ዝናብና በረዶ የሚኖርበት ቀዝቃዛ ወቅት ነው፡፡

ሰራዊቱን ሁሉ ይዞ ወደ ኢየሩሳሌም መጣ

‹‹ኢየሩሳሌም›› እዚያ የሚኖሩ ሰዎች ማለት ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹የኢየሩሳሌምን ሕዝብ ለመውጋት ሰራዊቱን ይዞ መጣ›› ወይም፣ ‹‹ኢየሩሳሌምን ድል ለማድረግ ሰራዊቱን ይዞ መጣ››

በአራተኛ ወር በዘጠነኛው ቀን

ይህ አራተኛ ወር በዕብራውያን ቀን አቆጣጠር ነው፡፡ በምዕራባውያን ቀን መቁጠሪያ ዘጠነኛው ቀን ሰኔ መጨረሻ ላይ ነው፡፡ ይህ ጥቂት ወይም ምንም ዝናብ የማይኖርበት ደረቅ ወቅት ነው፡፡

የምድሪቱ ሕዝብ

እነዚህ ጦርነቱ ሲጀመር ከአጐራባች ሰፈሮች ወደ ኢየሩሳሌም የሸሹ ስደተኞችን ጨምሮ የኢየሩሳሌም ነዋሪዎች ናቸው፡፡