am_tn/2ki/22/20.md

1.2 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ይህ በነቢዪት ሕልዳና በኩል ያህዌ ለንጉሥ ኢዮስያስ የላከው መልእክት ፍጻሜ ነው፡፡

ስለዚህ ወደ አባቶችህ እሰበስብሃለሁ፤ ወደ መቃብርህ በሰላም እሰበስብሃለሁ

ሁለቱም ዐረፍተ ነገሮች በመሠረቱ ተመሳሳይ ናቸው፡፡ ሁለቱም ትሞታለህ ማለት ናቸው አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ስለዚህ እንድትሞትና በሰላም እንድትቀበር አደርጋለሁ››

ዐይኖችህ አያዩም

እዚህ ላይ፣ ‹‹ዐይኖች አለማየታቸው›› መከራ አይደርስብህም ማለት ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹አይደርስብህም››

ዐይኖችህ

እዚህ ላይ፣ ‹‹ዐይኖች›› መላውን የሰው ሁለንተና ያመለክታል፡፡

በዚህ ቦታም የሚመጣውን መከራ

ያህዌ መከራ እንዲሆን ማድረጉ፣ ጥፋት ያህዌ ወደዚያ ቦታ የሚያመጣው ነገር እንደ ሆነ ተነግሯል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በዚህ ቦታ የሚመጣው ከባድ ነገር››