am_tn/2ki/22/14.md

1.5 KiB

ሕልዳና

ይህ የሴት ስም ነው

ሰሎም… ቲቁዌ… ሐርሐስ

እነዚህ የሰው ስሞች ናቸው

የአልባሳት ጠባቂው

ይህም ማለት 1) ካህናቱ ቤተ መቅደሱ ውስጥ የሚለብሷቸውን ልብሶች የሚጠብቅ፣ ወይም 2) የንጉሡን ልብሶች በአግባቡ የሚይዝ ማለት ሊሆን ይችላል፡፡

በሁለተኛው ሰፈር በኢየሩሳሌም ኖረች

እዚህ ላይ፣ ‹‹ሁለተኛው ሰፈር›› ከኢየሩሳሌም በስተ ሰሜን የተሠራውን አዲሱ የከተማው ክፍል ማለት ነው፡፡ ‹‹ሁለተኛ›› በተለምዶ 2 ማለት ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በኢየሩሳሌም በአዲሱ ሰፈር ኖረች››

ወደ እኔ ለላካችሁ ሰው

እዚህ ላይ፣ ‹‹ሰው›› ንጉሥ ኢዮስያስን ማለት ነው፡፡

በዚህ ቦታና በሕዝቡ ላይ ታላቅ ጥፋት አመጣለሁ

ያህዌ አስቸጋሪ ነገሮችን ማድረጉ፣ ሕዝቡ ላይ ጥፋት ማምጣት እንደ ሆነ ተነግሮአል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በዚህ ቦታና እዚህ በሚኖሩ ላይ ከባድ ችግር አመጣለሁ››

በዚህ ቦታ

‹‹በኢየሩሳሌም›› ይህ መላውን የይሁዳን ምድር የሚወክለውን የኢየሩሳሌምን ከተማ ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ይሁዳ ላይ››