am_tn/2ki/22/11.md

1.9 KiB

እንዲህም ሆነ

በቋንቋህ የታሪኩን መጀመሪያ ክፍል ለማመልከት የምትጠቀምበት ቃል ካለ እዚህ ተጠቀምበት፡፡

የሕጉን መጽሐፍ ቃል ሰማ

‹‹ቃል›› የሕጉን መልእክት ያመለክታል፤ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በመጽሐፉ ተጽፎ የነበረውን ሕግ ሰማ›› ወይም፣ ‹‹በጥቅልል መጽሐፍ የተጻፈውን ሕግ ሰማ››

ልብሱን ቀደደ

ይህ በጣም ማዘንን ወይም መተከዝን የሚያመለክት ድርጊት ነው፡፡

አኪቃም… ሰፋን… ዓክበር… ሚክያ… ዓሳያ

እነዚህ የሰው ስሞች ናቸው፡፡

ሂዱና ያህዌን ጠይቁ

የያህዌን ፈቃድ ለማወቅ ሰዎች ወደ ያህዌ ነቢዪት ሄደው እንዲጠይቁ ንጉሡ ማዘዙ እንደ ነበር 22፥14 ላይ ግልጽ ሆኗል፡፡

ጠይቁ

ወደ ሰው ሄዶ ምክር መጠየቅ

የዚህ የተገኘው መጽሐፍ ቃል

‹‹ቃል›› — ሕግን ይወክላል፡፡ ይህን በሌላ መልኩ ማስቀመጥ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ኬልቅያስ ባገኘው በዚህ መጽሐፍ ውስጥ ያለ ሕግ››

በእኛ ላይ የሚነደው የያህዌ ቁጣ ታላቅ ነውና

የያህዌ ቁጣ የሚነድ እሳት እንደ ሆነ ተነግሯል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ያህዌ በጣም ተቆጥቶናል››

እኛን በተመለከተ የተጻፈው

ይህ የሚያመለክተው ለእስራኤል የተሰጠውን ሕግ ነው፡፡ ይህን በሌላ መልኩ ማስቀመጥ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እንድናደርገው ሙሴ በሕጉ የጻፈው ሁሉ›› ወይም፣ ‹‹በሙሴ በኩል ያህዌ ለእስራኤል የሰጠው ሕግ ሁሉ››