am_tn/2ki/22/01.md

1.5 KiB
Raw Permalink Blame History

ሠላሳ አንድ ዓመት

31 ዓመት››

ይዲዳ

ይህ የሴት ስም ነው፡፡

አዳያ

ይህ የሰው ስም ነው፡፡

ባሱሮት

ይህ ይሁዳ ውስጥ ያሉ ከተማ ስም ነው

በያህዌ ዐይን ፊት መልካም ነገር አደረገ

‹‹ዐይን›› የያህዌን ሐሳብ ወይም ስለ ነገሮች ያለውን ግንዛቤ ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ያህዌ መልካም ነው የሚለውን አደረገ›› ወይም፣ ‹‹ያህዌ እንደሚያስበው መልካም ነገር አደረገ››

አባቱ ዳዊት በሄደበት መንገድ ሁሉ ሄደ

‹‹አባቱ ዳዊት በሄደበት መንገድ ሁሉ ሄደ›› ኢዮስያስ ዳዊት እንዳደረገው ማድረጉ ዳዊት በሄደበት መንገድ መሄዱ እንደሆነ ተነግሮአል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹አባቱ ዳዊት በኖረበት መንገድ ኖረ›› ወይም፣ ‹‹አባቱ የዳዊትን ምሳሌ ተከተለ››

ወደ ቀኝም ወደ ግራም አላለም

ሙሉ በሙሉ ለያህዌ መታዘዝ ለአንድ ሰው በትክክለኛው መንገድ መሄድና ከዚያም ወደ ኃላ አለማለት እንደ ሆነ ተነግሯል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ምንም ያህዌን ደስ የማያሰኝ ነገር አላደረገም›› ወይም፣ ‹‹ለያህዌ ሕግ ሙሉ በሙሉ ታዘዘ››