am_tn/2ki/18/31.md

791 B

ከእኔ ጋር ሰላም መሥርቱ፤ እጃችሁን ስጡ

‹‹ከከተማው ወጥታችሁ እጃችሁን ስጡኝ›› ወይም፣ ‹‹እጃችሁን ለመስጠት ከእኔ ጋር ተስማሙ፤ ከከተማ ወጥታችሁ ወደ እኔ ኑ››

ከገዛ ወይኑ.. ከገዛ በለሱ… ከገዛ ጉድጓዱም ውሃ

እነዚህ የምግብና ውሃ መገኛዎች ሰላምንና መተረፍረፍን ይወክላሉ፡፡ ይህ ይህን ሐሳብ ለመግለጽ የተለመደ አባባል ነው፡፡

እህልና አዲስ የወይን ጠጅ… እንጀራና የወይን እርሻ… የወይራ ፍሬና ማር

ይህ የመልካምና በየዕለቱ ሕይወት የበዛ ነገር የማግኘት ምሳሌ ነው፡፡