am_tn/2ki/18/26.md

1.2 KiB

ኤልያቂም… ኬልቅያስ… ሰምናስ… ዮአስ

የእነዚህን ሰዎች ስም 2 ነገሥት 18፥18 ላይ እንደ ተረጐምህ ተርጉመው፡፡

ቅጥሩ ላይ ባሉ ሰዎች ጆሮ

‹‹ጆሮ›› የመስማት ችሎታን ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በቅጥሩ ላይ ያሉ ሰዎች ሰምተው እንዳይፈሩ››

ጌታዬ ይህን እንድናገር የላከኝ ለጌታችሁና ለእናንተ ብቻ ነውን? እነርሱም እንደ እናንተው ገና ኩሳቸውን ይበሉ ዘንድ፣ ሽንታቸውንም ይጠጡ ዘንድ በቅጥሩ ላይ ለተቀመጡት ጭምር አይደለምን?

ይህን የጠየቀው አድማጮቹ መልሱን እንዲሚያውቁ በማሰብ ሲሆን፣ ፍላጐቱ የኢየሩሌምን ሕዝብና መሪዎች ማዋረድና ድል ማድረግ መሆኑን አጽንዖት ለመስጠት ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ጌታዬ የላከኝ ወደ እናንተና ወደ ጌታችሁ ብቻ ሳይሆን፣ በሕይወት ለመኖር የገዛ ኩሳቸውን ለሚበሉና የገዛ ሽንታቸውን ለሚጠጡት ለዚህ ከተማ ሰዎች ጭምር ነው››