am_tn/2ki/15/34.md

2.7 KiB

በያህዌ ዐይን ፊት መልካም ነገር

ዐይን ዕይታን ይወክላል፤ ዕይታ ደግሞ ሐሳብን ወይም ፍርድን ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በያህዌ ፍርድ መልካም ነገር›› ወይም፣ ‹‹ያህዌ መልካም የሚለውን ነገር››

ኮረብቶች ላይ ያሉ ማምለኪያዎችን አላስወገደም

ይህን በሌላ መል ማስቀመጥ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ማንም የኮረብቶቹን ማምለኪያዎች አላስወገደም›› ወይም፣ ‹‹ኢዮአታም የኮረብቶቹን ማምለኪያዎች ማንም እንዲያስወግድ አላደረገም››

አልተወገዱም

መወገድ መደምሰስን ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹አልተደመሰሱም››

ኢዮአታም የላይኛውን በር መልሶ ሠራ

‹‹ኢዮአታም ሠራ›› የሚለው የኢዮአታም ሠራተኞች መሥራታቸውን ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ኢዮአታም ሠራተኞቹ የላይኛውን በር እንዲሠሩ አደረገ››

በይሁዳ… ተጽፎ የሚገኝ አይደለምን?

ጥያቄው የቀረበው ኢዮአታምን በተመለከተ መረጃ በዚህ ሌላ መጽሐፍ ውስጥ እንደሚገኝ ለአንባቢው ለማሳሰብ ነው፡፡ 2 ነገሥት 8፥23 ላይ ያለውን እንዴት እንደ ተረጐምኸው ተመልከት፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በይሁዳ ነገሥታት ታሪክ መጽሐፍ ተጽፎአል››

በዚያ ዘመን

ይህ አንድ ወቅትን ያመለክታል፡፡ ይህ ወቅት የትኛው እንደ ነበር የበለጠ ግልጽ ማድረግ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በዚያ ጊዜ›› ወይም፣ ‹‹ኢዮአታም የይሁዳ ንጉሥ በነበረ ጊዜ››

ረአሶን

ይህ የሰው ስም ነው፡፡

ፋቁሔ… ሮሜልዩ

እነዚህ የሰው ስሞች ናቸው፡፡ ፋቁሔ የእስራኤል ንጉሥ ነበር፡፡ 2 ነገሥት 15፥37 ላይ ይህን እንዴት እንደተረጐምኸው ተመልከት፡፡

ኢዮአታም ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ

አንቀላፋ ሞተ ማለት ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ኢዮአታም እንደ አባቶቹ ሞተ›› ወይም፣ ‹‹አባቶቹ እንደ ሞቱ ኢዮአታምም ሞተ››

በእግሩ ተተክቶ ነገሠ

‹‹በእግሩ ተተክቶ›› የሚለው ሐረግ፣ ‹‹በእርሱ ቦታ›› ማለት ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በኢዮአታም ቦታ ነገሠ››