am_tn/2ki/15/29.md

2.5 KiB

በእስራኤል ንጉሥ በፋቁሔ ዘመን

ይህ የሚያመለክተው የፋቁሔን የግዛት ዘመን መሆኑን በግልጽ ማስቀመጥ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ንጉሥ ፋቁሔ የእስራኤል ንጉሥ በነበረበት ዘመን›› ወይም፣ ‹‹በእስራኤል ንጉሥ በፋቁሔ ዘመን››

ቴልጌል-ቴልፌልሶር

2 ነገሥት 15፥19 ላይ ይህ ሰው፣ ‹‹ፑል›› ተብሎአል፡፡

ዒዮን… አቤልቤትመዓካን… ያኖን… ቃዴስ… ሐጾር… ገለዓድ… ገሊላ…

እነዚህ የከተሞች ወይም የክልሎች ስሞች ናቸው፡፡

ሕዝቡን ወደ አሦር ወሰደው

እዚህ ላይ፣ ‹‹እርሱ›› የሚያመለክተው ቴልጌል-ቴልፌልሶርን ሲሆን፣ እርሱንና ሰራዊቱን ይወክላል፡፡ ሕዝቡን ወደ አሦር መውሰድ ወደ አሦር እንዲሄዱ ማስገደድን ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እርሱና ሰራዊቱ ወደ አሦር እንዲሄድ ሕዝቡን አስገደዱ››

ሕዝቡ

የትኛው ሕዝብ እንደ ሆነ ግልጽ ማድረግ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በእነዚህ ቦታዎች የነበረ ሕዝብ›› ወይም፣ ‹‹የእስራኤል ሕዝብ››

ሆሴዕ… ኤላ

እነዚህ የሰዎች ስሞች ናቸው፡፡

አሤረበት

ሤራ ሰው ወይም አንዳች ነገር ላይ ጉዳት ለማድረስ ድብቅ ዕቅድ ማለት ነው፡፡

አደጋ ጥሎ ገደለው

‹‹ሆሴዕ ፋቁሔ ላይ አደጋ ጥሎ ገደለው››

በእግሩ ተተክቶ ነገሠ

‹‹በእግሩ ተተክቶ›› የሚለው ሐረግ፣ ‹‹በእርሱ ቦታ›› ማለት ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በፋቁሔ ቦታ ነገሠ››

የዖዝያን ልጅ ኢዮአታም በነገሠ በሃያኛው ዓመት

ይህ የአገዛዙ ሃያኛው ዓመት መሆኑን ይበልጥ ግልጽ ማድረግ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹የዖዝያን ልጅ ኢዮአታም በነገሠ በ20ኛው ዓመት››

በእስራኤል ነገሥታት ታሪክ መጽሐፍ ተጽፎ ይገኛል

ይህን በሌላ መልኩ ማስቀመጥ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ይህን በተመለከተ በእስራኤል ነገሥታት ታሪክ መጽሐፍ ማንበብ ትችላላችሁ››