am_tn/2ki/15/27.md

1.1 KiB

የይሁዳ ንጉሥ ዓዛርያስ በነገሠ በአምሳኛው ሁለተኛው ዓመት

ይህ በእርሱ አገዛዝ አምሳ ሁለተኛው ዓመት መሆኑን በግልጽ ማስቀመጥ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በይሁዳ ንጉሥ ዓዛርያስ 52ኛ ዓመት››

በያህዌ ዐይን ፊት ክፉ ነገር አደረገ

የያህዌ ዐይን የያህዌን ፍርድ ይወክላል፡፡ 2 ነገሥት 3፥2 ላይ ይህን እንዴት እንደ ተረጐምኸው ተመልከት፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በያህዌ ፍርድ ክፉ ነገር›› ወይም፣ ‹‹ያህዌ ክፉ ነው የሚለውን››

ከናባጥ ልጅ ኢዮርብዓም ኀጢአት አልተመለሰም

ከኀጢአት መመለስ ያንን አለማድረግ ማለት ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ዘካርያስ የናባጥ ልጅ የኢዮርብዓምን ኀጢአት ለማድረግ እንቢ አላለም›› ወይም፣ ‹‹የናባጥ ልጅ ኢዮርብዓምን ኀጢአት አደረገ››