am_tn/2ki/15/19.md

1.9 KiB
Raw Permalink Blame History

የአሦር ንጉሥ ቴልጌልቴልፌልሶር ምድሪቱን ወረረ

‹‹የአሦር ንጉሥ ቴልጌልቴልፌልሶር›› የሚለው ቴልጌልቴልፌልሶርንና ሰራዊቱን ይወክላል

በምድሪቱ መጣ

‹‹በምድሪቱ መጣ›› የሚለው ምድሪቱን ለመውረር ለማለት ነው፡፡ ‹‹ምድሪቱ›› የእስራኤልን ምድር ሲሆን እዚያ የሚኖሩ ሰዎችን ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹የእስራኤልን ሕዝብ ለመውረር ከሰራዊቱ ጋር መጣ››

አንድ ሺህ መክሊት ብር

1000 መክሊት ብር›› ይህን ወደ ዘመኑ ምንዛሬ መለወጥ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ሠላሳ ሦስት ኪሎ ግራም ብር›› ወይም፣ ‹‹ሠላሳ ሦስት ሜትሪክ ቶን ብር››

የቴልጌልቴልፌልሶር ርዳታ ለማግኘት

‹‹ርዳታ›› የሚለውን፣ ‹‹ድጋፍ›› በማለት መተርጐም ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ቴልጌልቴልፌልሶር እንዲደግፈው››

የእስራኤልን መንግሥት በእጁ ለማጽናት

የእስኤልን መንግሥት በእጁ ማጽናት መንግሥቱን መግዛት ማለት ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በእስራኤል መንግሥት ላይ አገዛዙን ለማጠናከር››

ይህን ገንዘብ ከእስራኤል ሰበሰበ

‹‹ይህን ገንዘብ ከእስራኤል ወሰደ››

አምሳ ሰቅል ብር

ይህን ወደ ዘመኑ ምንዛሬ መለወጥ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ስድስት መቶ ግራም ብር›› ወይም፣ ‹‹የኪሎ ግራም ሦስት አምስተኛ ብር››

በዚያች ምድር አልቆየም

‹‹በእስራኤል ምድር አልቆየም››